# ቤዛነት፥ቤዛ “ቤዛ” እና “ቤዛነት” ለሰው ልጆች ኃጢአት የሚከፈልና የእርሱን በኃጢአት መቆጣት የሚያበርድ መሥዋዕት እግዚአብሔር ያዘጋጀበትን ሁኔታ ያመለክታል * በብሉይ ኪዳን ዘመን እንስሳን በመግደል ለእስራኤላውያን ኃጢአት የደም መሥውዕትን በማቅረብ ጊዜያዊ ቤዛ እንዲደረግ እግዚአብሔር ፈቅዶ ነበር * በአዲስ ኪዳን እንደተጻፈው እውነተኛና ዛላቂ የኃጢአት ቤዛ የክርስቶስ መስቀል ላይ ሞት ብቻ ነው * ክርስቶስ የሞት ጊዜ ከኃጢአታቸው የተነሣ ሰዎች ሊቀበሉት ይገባ የነበረውን ቅጣት ወሰደ። በመሥዋዕታዊ ሞቱ የቤዛነት ዋጋ ከፈለ።