# ሐዋርያ ፣ ሐዋርያነት ሐዋርያት ስለ እግዚአበሔር ስለ መንግሥቱ ለሰዎች እንዲሰበኩ እየሱስ የላካቸው ሰዎች ነበሩ፤ሐዋርያነት የሚለው ቃል ሐዋርያነት ለመሆን የተመረጡ ሰወች የነበራቸውን ቦታና ስልጣን ያመለክታል። * ሐዋርያ የሚለው ቃል ለአንድ ለተለየ ዓላማ የተላከ ማለት ነው፤ሐዋርያ እርሱን የላከው ሥልጣን አለው። * ለእየሱስ በጣም ቅርበ የነበሩ አሥራ ሁለት ደቀመዛሙርት የመጀመሪዎቹ ሐዋርያት ሆኑ፤ጻውሎስንና ያዕቆበን የመሳሰሉ ሰዎችም ሐዋርያት ሆነዋል። * በእግዚአብሔር ሓይል ሐዋርያት አጋንንት ከሰዎች እንዲወጡ ማዘዝን ጨምሮ በድፍረት ወንጌልን ሰብከዋል፤የታመሙትን ፈውሰዋል።