# ዝሙት፣ዘማዊነት፣ዘማዊ፣ዘማዊት “ዝሙት” አንድ ያገባ ሰው የትዳር ጓደኛው ካልሆነች ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸምን ኃጢአት ያመለክታል። “ዘማዊነት”የዚህ ዐይነት ተግባርን ወይም ይህን ኃጢያት የሚያደርግ ሰው ድትጊት ያመለክታል። * አንዳንዴ “ዘማዊት” የሚለው ቃል ዝሙት የፈጸመችው ሴት መሆንዋን ለይቶ ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል። * ዝሙት ባልና ሚስት በጋብቻ ኪዳን አንዳቸው ለሌላው ያገቡትን ቃል ያፈርሳል። * ዝሙት እንዳያደርጉ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዝዟል። * ብዙውን ግዜ ዘማዊነት የሚለው ቃል የእስራኤል ሕዝብ ለእግዚአብሔር ታማኝ ያልሆኑበትን በተለይ ደግሞ ሐሰተኛ አማልክትን ያመለከበትን ሁኔታ ለመግለጽ ምሳሌያዊ በሆነ ቋንቋ ጥቅም ላይ ውሏል።