# ዕጣን ዕጣን ከዛፍ ሙጫ የሚገኝ ጣፋጭ ሽታ ያለው ቅመም ነው። ሽቱኑ ሌላም ጣፋጭ መዓዛ ያለው ነገር ለመሥራት ያገለግላል። * የሞተ ሰው አካልን ለመቃብር ለማዘጋጀት የሚያገለግል ጠቃሚ ቅመም ነው። ተፈጥሮአዊ ፈስውና መረጋጋት ያስገኛል። * ሕፃኑ ኢየሱስን በኢየሩሳሌም ለማየት ከምሥራቅ የመጡት ጠቢባን ይዘውይ ከነበረ ሦስት ስጦታ አንዱ ዕጣን ነበር። ነጻ መሆን፣ ነጻነት፣ አርነት “ነጻ መሆን” ወይም፣ “ነጻነት” ባርያ አለመሆንን በምንም ዓይነት ቀንበር ሥር አለመሆንን ያመለክታል። * “አርነት” የሚለውም ቃል፣ “ነጻነት” ከሚለው ጋር አንድ ትርጕም አለው። * “ነጻ ማድረግ” ወይም፣ “ነጻ ማውጣት” የተሰኘው አገላለጽ ከእንግዲህ ከባርነት ወይም ቀንበር ሥር እንዳይሆን ማድረግ ማለት ነው። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እነዚህ ቃሎች ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉት በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች ከእንግዲህ ከኃጢአት ኀይል በታች አለመሆናቸውን በሚያመለክት ምሳሌያዊ አነጋገር ነው። * “አርነት መውጣት” ወይም በመንፈስ ቅዱስ ትምህርትና ምሪት ነጻ ሆኖ መኖር እንጂ፣ “ነጻነት” ከእንግዲህ የሙሴን ሕግ ከመጠበቅ ግዴታ ነሣ መሆንንም ሊያመለክት ይችላል።