# መወሰን፣ የተወሰነ “መወሰን” እና፣ “የተወሰነ” የተሰኙት ቃሎች አንድ ነገር ከመሆኑ በፊት እንደዚያ እንዲሆን መቁረጥን ወይም ማቀድን ያመለክታሉ። * ብዙውን ጊዜ ቃሉ የዘላለምን ሕይወት እንዲያገኙ እግዚአብሔር ሕዝቡን መወሰኑን ያመለክታል። * አንዳንዴ፣ “ማቀድ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ይውላል፤ ያም አንድ ነገር ከመሆኑ በፊት አስቀድሞ መቁረጥን ነው የሚያመለክተው። መንጠቅ፣ ንጥቂያ “መንጠቅ” የሚያመለክተው አንድን ነገር፣ ብዙውን ጊዜ ደግሞ ለምግብ የሚሆን እንስሳን ማደንን ነው። * ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ሲውል ጥቅሙን እንዲያጣ የተደረገውን፣ የእርሱ የሆነው አለአግባብ የተወሰደበትን ወይም በሌላ ኀያል በሆነ ሰው የሚጨቆን ሰውን ያመለክታል። * ሰዎች ላይ የሚፈጸም፣ “ንጥቂያ” እነርሱን በመጫን ወይም ከእነርሱ በመስረቅ የእነርሱን ጥቅም መውሰድ ማለት ነው።