# ምስክር፣ የዓይን ምስክር “ምስክር” የሆነውን ነገር በግል የሚያውቅ ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ ምስክር የሚባለው እውነት መሆኑን የሚያውቀውን የሚናገር ሰው ነው። “የዓይን ምስክር” እዚያ የነበረና የሆነውን ሁሉ በዓይኑ የተመለክተ ሰው ነው። * አንድን ነገር፣ “መመስከር” የሆነውን ነገር ማየት ማለት ነው። * ምስክር፣ ፍርድ ቤት ቀርቦ ሲሆን ያየውን ወይም የሰማውን ይመሰክራል። * ምስክሮች ስላዩትና ስለሰሙት እውነቱን መናገር ይጠበቅባቸዋል * እውነቱን የማይናገር ምስክር፣ “የሐሰት ምስርክ” ይባላል። * “በመካከላችን ይመስክር” ማለት በመካከላችን ስለ ተደረገው ውል ማስረጃ ይሁን ማለት ነው። ምስክሮች እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን እያደረገ መሆኑን ያረጋግጣሉ።