# መርዳት፣ የተረዳ “መረዳት” መረጃ መስማት ወይም መቀበልና ምን ማለት እንደሆነ መገንዘብ ማለት ነው። * “መረዳት” የሚለው ቃል፣ “ዕውቀትን” ወይም፣ “ጥበብን” ወይም አንድን ነገር እንዴት ማድረግ እንደሚቻል መገንዘብን ያመለክታል። የአንድን ሰው ስሜት ማወቅንም ይጨምራል። * በኤማሁስ መንገድ እየሄዱ በነበረ ጊዜ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ መሲሑን በተመለከተ የተነገሩ ቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጕም እንዲረዱ አደረገ። * እንደ ዐውዱ አገባብ፣ “መረዳት” የሚለው፣ “ማወቅ” ወይም፣ “ማመን” ወይም፣ “መገንዘብ” ወይም፣ “ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። * ብዙ ጊዜ፣ “መረዳት” – “ዕውቀት” ወይም፣ “ጥበብ” ተብሎ ይተረጎማል።