# እርድ ብዙውን ጊዜ “ጭፍጨፋ” በአንድ ጊዜ ብዙ እንስሳት ወይም ሰዎችን መግደል ወይም በአሰቃቂ ሁኔታ መግደል ነው። ማረድ በሚለው ቃል ከተጠቀምን ደግሞ ለመብል እንዲሆኑ ጥቂት እንስሳትን መግደልም ይሆናል * አብርሃም ምድረ በዳ ውስጥ በነበረ ድንኳኑ ሦስት እንግዶች ተቀብሎ ነበር፤ ያማረውን ወይፈን አርደው ለእንግዶቹ መልካም ምግብ እንዲያዘጋጁ አገልጋዮቹን አዘዘ * ቃሉን የማይከተሉትን ሁሉ እንዲገድሉ (እንዲጨፈጭፉ) እግዚአብሔር መልአኩን እንደላከ ነቢዩ ሕዝቅኤል አመልክቷል * 1ሳሙኤል እግዚአብሔር ላይ በማመፃቸው 30,000 የሚሆኑ እስራኤላውያን በጠላቶቻቸው ስለተገደሉበት ጭፍጨፋ ይናገራል * ይህ ቃል፣ “መግደል” ወይም፣ “ማረድ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል