# ዕፍረት፣ አሳፋሪ፣ አፈረ ዕፍረት አንድ ሰው ወይም ሌላው ካደረገው መጥፎ ወይም ተገቢ ያልሆነ ነገር የተነሣ የሚደርስ ውርደት ወይም ጥሩ ስሜት እንዳይኖር የሚያደርግ ሕመም ነው * “አሳፋሪ” ነገር ተገቢ ያልሆነ ወይም፣ የሚያዋርድ ነገር ነው * “አፈረ” የሚለው አንድ ሰው መጥፎ ወይም ተገቢ ያልሆነ ነገር ሲያደርግ የሚሰማውን ስሜት ያመለክታል * “ማሳፈር” – ማሸነፍ ወይም ውርደት እንዲሰማቸው ኅጢአታቸውን መግለጥ ማለት ነው * ነቢዩ ኢሳይያስ ጣዖት የሚሠሩና የሚያመልኩ እንደሚያፍሩ ይናገራል * አንድ ሰው ከኅጢአቱ በንስሐ ካልተመለሰ ኅጢአቱን በመግለጥና እርሱን በማዋረድ ያንን ሰው እግዚአብሔር ያሳፍረዋል