# ሴላ ሴላ ብዙውን ጊዜ መዝሙር መጽሐፍ ውስጥ የሚገኝ የዕብራይስጥ ቃል ነው በርካታ ትርጉሞች ይኖሩት ይሆናል * ጉባኤው የተነገረውን ረጋ ብሎ እንዲያስብ ጥሪ ለማቅረብ የታሰበ፣ “ረጋ በል፤ አመስግን” ማለት ሊሆን ይችላል * መዝሙሮቹ የተጻፉት በጉባኤ እንዲዘመሩ በመሆኑ ዘማሪው ዝም እንዲልና የሙዚቃ መሣሪያው ብቻ እንዲጫወት ወይም አዳማጮቹ የመዝሙሩን ቃሎች በሚገባ እንዲያስቡ የሚያመለክት ሙዚቃዊ ቋንቋ ሊሆን ይችላል