# የባሕር አውሬ “የባሕር አውሬ” ውቅያኖስ ወለል ላይ ያሉትን የባሕር ሣሮችንና ተክሎችን የሚበላ ግዙፍ የባሕር እንስሳ ነው * ይህ ግራጫና ጠንካራ ቆዳ አለው። እንደ እጅና እግር በሚጠቀምባቸው የአካል ክፍሎቹ ባሕር ውስጥ ይንቀሳቀሳል * በጥንት ዘመን ሰዎች የባሕር አውሬን ቆዳና ሌጦ ድንኳን ለመሥሪያ ይጠቀሙበት ነበር። ይህ ቆዳ የመገናኛውን ድንኳን የላይኛውን ክፍል ለመሸፈኛነትም ይጠቅም ነበር * እንደ ላም ሣር ስለሚበላ አንዳንድ ሰዎች፣ “የባሕር ላም” በማለት ይጠሩታል፤ በሌሎች ብዙ ነገሮች ግን አይመሳሰሉም