# ንጉሣዊ “ንጉሣዊ” የሚለው ቃል ከንጉሥ ወይም ከልዕልት ጋር የተያያዙ ሰዎችንና ነገሮችን ማለትም ዙፋናቸውን፣ ቤተ መንግሥታቸውን፣ ልብሶቻቸውንና ልጆቻቸውን ይመለክታል። * “ንጉሣዊ” ተብሎ ለሚጠሉ ነገሮች ምሳሌ የሚሆኑን ነገሮች የንጉሥ ልጆችን፣ ልብሶችን፣ ቤተ መንግሥቶችን፣ ዙፋኖችንና አክሊሎችንም ያካትታል። * ቤተ መንግሥት ንጉሥ ወይም ንግሥት የሚኖሩበት በጣም የሚያምር ልዩ መኖሪያ ነው። * ንጉሡ፣ አንዳንዴ “ንጉሣዊ” ልብስ ተብሎ የሚጠራ ልዩ ልብስ ይለብሳል። ብዙ ጊዜ ንጉሥ በጣም ውድ የሆነውንና በቅ አላሉ የማይገኘውን ሐምራዊ ቀለም የተነከረ ልብስ ይለብሳል።