# ካባ ካባ ወንዶችም ሆነ ሴቶች የሚለብሱት እጅጌ ረጃጅም ከውጭ የሚደረብ ልብስ ነው። ከኮት ጋር ይመሳሰላል። * ካባ ከፊት ለፊቱ ክፍት ሲሆን፣ በመታጠቂያ ወይም በቀበቶ ታስሮ ይገጠማል። * ቁመታቸው ረጅም ወይም አጭር ሊሆን ይችላል። * ሐምራዊ ካባ የንጉሣዊነት፣ የሀብትና የታዋቂነት መገለጫ እንዲሆን የሚለብሱት ንጉሦች ነበር።