# ዕረፍት “ዕረፍት” የሚለው ቃል ዘና ለማለትና ኀይልን ለማደስ የሚሠሩትን ማቆም ማለት ነው። * አንድ ነገር፣ “ዐርፏል” ከተባለ፣ እዚያ ቦታ ቆሟል ወይም ተቀምጧል ማነት ነው። * “ያረፈች” ጀልባ ቀዘፋ ላይ ያልሆነች፣ ይልቁን ወደቡ ላይ አርፋ የቆመች ማለት ነው። * ሰዎች ወይም እንስሳት አርፈዋል ከተባለ ራሳቸውን ዘና ለማድረግ ተቀምጠዋል ወይም ተጋድመዋል ማለት ነው። * በሳምንቱ ሰባተኛ ቀን እንዲያርፉ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዟል። ያ ምንም ሥራ የማይሠራበት ቀን፣ “ሰንበት” ይባላል።