# መቀበል “መቀበል” የተሰጠ ወይም የቀረበ ነገርን ተቀብሎ የራስ ማድረግ ማለት ነው። * “መቀበል” የበደልን ወይም የኀጢአትን ቅጣት መውሰድ ማለትም ይሆናል። * ሰውን፣ “መቀበል” የሚቻልበት ሁኔታም አለ። ለምሳሌ፣ እንግዶችን ወይም ጎብኚዎችን “መቀበል” በመልካም ሁኔታ እነርሱን ማስተናገድና በተቻለ መጠን ምቾታቸውን መጠበቅ ማለት ነው። * “የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ መቀበል”፣ መንፈስ ቅዱስን ወደ ሕይወታችን ማስገባትና በእኛና በእኛ በኩል እንዲሠራ መፍቀድ ማለት ነው። * “ኢየሱስን መቀበል” በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የእግዚአብሔርን ድንቅ ስጦታ መቀበል ማለት ነው።