# መነፋት “መነፋት” የሚለው ፈሊጣዊ ቃል የሚያመለክተው ትዕቢተኛ ወይም ዕብሪተኛ መሆንን ነው። * ይህ ቃል ከሌሎች እበልጣለሁ የማለት ዝንባሌን ወይም ስሜት ያመለክታል። * ብዙ መረጃዎች ወይም ሐቆችን ማወቅ ወደ መነፋት ወይም ወደ ትዕቢት ሊያደርስ እንደሚችል ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ጽፏል።