# ማረሻ “ማረሻ” አንድን ቦታ ለዘር ለማዘጋጀት መሬቱን ሥርዓት ባለው መልኩ ለመቆፈር የሚያገለግል የእርሻ መሣሪያ ነው። * ማረሻ ጠለቅ ብሎ መሬቱን ለመቆፈር የሚረዳ ሹል ጫፍ አለው። ትልሙን ማስተካከል እንዲቻል ገበሬው የሚይዘው እጀታ አለው። * ብዙውን ጊዜ ማረሻ የሚጎተተው በሁለት በሬዎች ወይም ሌሎች እንስሳት ነው። * ጫፉ ላይ ብረት ወይም ሌላ ሹል ነበር ከመግባቱ ውጪ አብዛኛውን ጊዜ ማረሻ የሚሠራው ከጠንካራ እንጨት ነው።