# የኅብረት መሥዋዕት “የኅብረት መሥዋዕት” እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡ ከታዘዙት በርካታ የመሥዋዕት ስጦታዎች አንዱ ነበር። “የምስጋና መሥዋዕት” ወይም፣ “የሰላም መሥዋዕት” ተብሎም ይጠራል። * ይህ መሥዋዕት ምንም ጉድለት የሌለበት እንስሳ መሥዋዕት ማቅረብን፣ ደሙን መሠዊያው ላይ መርጨትንና በተለያየ ሁኔታ የተቀረውን የእንስሳውን አካልና ስቡን ማቃጠልንም ይጨምራል። * ከዚህ በተጨማሪ በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ የሚቃጠለውን እርሾ ያለበትና የሌለበት እንጀራም መሥዋዕት ይቀርባል። * ካህኑና መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ሰው የቀረበውን መሥዋዕት እንዲበሉ ይፈቀድላቸዋል።