# አረማዊ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “አረማዊ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ያህዌን ሳይሆን ሐሰተኛ አምላኮችን የሚያመልኩ ሰዎች ለማመልከት ነበር። * ከእነዚያ ሰዎች ጋር የተያያዘ ማንኛውም ነገር ማለትም የሚያመልኩበት መሠዊያ፣ የሚፈጽሙት ሃይማኖታዊ ሥርዓትና እምነታቸው ጭምር፣ “አረማዊ” ይባላል። * የአረማውያን እምነት ተፈጥሮን ወይም ከአንዱ እውነተኛ አምላክ ከያህዌ ውጪ ብዙ አምላኮች ማምለክንም ይጨምራል። * አንዳንድ የአረማውያን ሃይማኖቶች የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚደረግበት አምልኮን ወይም እንደ አንድ የአምልኳቸው ክፍል ሰዎችን መሥዋዕት ማቅረብንም ያካትታል።