# መሐላ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት አንዳች ነገር ለማድረግ የሚሰጥ ውል ያለው ተስፋ ቃል ነው። መሐላ የሚያደርግ ሰው የሰጠውን ተስፋ የመፈጸም ግዴታ አለበት። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “መሐላ” ቃል መግባት ማለት ነው። * “በ . . . መማል” ከተባለ መሐላው የሚደረግበት መሠረት ወይም ሥልጣን እንዲሆን የአንድን ሰው ስም በመጥራት በይፋ መናገር ማለት ነው። * አንዳንዴ ቃሉ፣ “መሐላ መማል” በሚል መልኩ ይቀርባል። * የጉድጓድ ውሃ አጠቃቀምን በተመለከተ ኪዳን ለማድረግ አብርሃምና አቢሜሌክ ተማምለው ነበር። * ከአብርሃም ዘሮች መካከል ለልጁ ለይስሐቅ ሚስት እንዲፈልግለት አብርሃም አገልጋዩን ቃል አስገብቶት ወይም አስምሎት ነበር። * ለሕዝቡ የገባውን ተስፋ ለመፈጸም እግዚአብሔር ራሱ ምሎ ነበር። * በዚህ ዘመን፣ “መሐላ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የሚውልበት ሁኔታ እንዲሁ ከንቱ ቃል መናገር ሲሆን፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕም ጋር አይስማማም።