# አእምሮ (ልብ) አእምሮ የሚያስብና ውሳኔ የሚያደርግ የሰው ተፈጥሮ ክፍል ነው። * የሰው አንጎል ቁሳዊ የማሰቢያ አካል ነው። * የእያንዳንዱ ሰው አእምሮ የእርሱ ወይም የእርሷ ሐሳብና አመክንዮ ሁለንተና ነው። * “የክርስቶስ አእምሮ (ልብ)” ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያስበውና እንደሚያደርገው ማሰብና ማድረግ ማለት ነው። ይህንንም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ለክርስቶስ ትምህርት በመገዛት ለእግዚአብሔር አብ መታዘዝ ማለት ነው።