# ብልት፣ ክፍል ብልት ወይም ክፍል የአንድ ሕንፃ፣ አካል ወይም ቡድን አንድን ክፍል ያመለክታል። * አዲስ ኪዳን ክርስቲያኖችን የክርስቶስ አካል፣ “ብልቶች” ይላቸዋል። በክርስቶስ የሚያምኑ ከተለያዩ ብዙ ብልቶች የተሠራው አካል ወገን ናቸው። * ኢየሱስ ክርስቶስ የአካሉ፣ “ራስ” ሲሆን እያንዳንዱ አማኝ እንደ አካሉ ብልቶች ይሠራሉ። መላው አካል በሚገባ መሥራት እንዲችል መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዱ የአካሉ ብልት ትክክለኛ ቦታውን ይሰጠዋል። * የአይሁድ ሸንጎና የፈሪሳውያንን በመሳሰሉ ቡድኖች ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው ግለ ሰቦች የእነዚያ ቡድኖች “ብልቶች” ተብለዋል።