# አንበሳ አንበሳ እጁ የገባውን የሚገድልበትና የሚግነጣጥልበት ጥርሶችና ጥፍሮች ያሉት ባለ አራት እግር ትልቅ የዱር አውሬ ነው። * አንበሶች የሚያድኑትን እንስሳ ለመያዝ የሚያስችላቸው ብርቱ አካልና ታላቅ ፍጥነት አላቸው። * ወንዶቹ አንበሶች ራሳቸው ዙሪያ ጎፈር አላቸው። * አንበሶች ለምግብ ሌሎች እንስሳትን ይገድላሉ፤ ለሰዎችም ቢሆን አደገኛ ሊሆኑይችላሉ። * ንጉሥ ዳዊት ወጣት በነበረ ጊዜ ይጠብቃቸው የነበሩ በጎች ለመታደግ አንበሶች ገድሎ ነበር።