# ደብዳቤ፣ መልእክት ደብዳቤ ብዙ ጊዜ ከጸሐፊው ርቀው ላሉ ወገኖች ወይም ሰዎች የሚላክ መልእክት ነው። መልእክት የተለየ ዐይነት ደብዳቤ ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ የሚጻፈው ማስተማርን ለመሰሉ የተለዩ ዓላማ ነው። * አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን መልእክቶችና ሌሎች ደብዳቤዎች ይጻፉ የነበረው ከእንስሳት ቆዳ ከሚሠራ ብራና ወይም ፓፒረስ በሚባል ተክል ልጥ ላይ ነበር። * መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ጳውሎስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብ፣ ይሁዳና ጴጥሮስ በመላው የሮም መንግሥት የተለያዩ ከተሞች ውስጥ የነበሩ የጥንት ክርስቲያኖችን ለማበረታታትና ለማጽናናት መልእክቶች ጽፈው ነበር።