# መንግሥት መንግሥት በንጉሥ የሚገዛ የሰዎች ቡድን ነው። ንጉሥ ወይም ሌሎች ገዦች የሚቆጣጠሩትና በሥልጣን የሚያስተዳድሩትንም አካባቢ ወይም ፖለታካዊ አገርንም ያመለክታል። * መንግሥት ማንኛውም ዐይነት መልክዓ ምድራዊ መጠን ሊኖረው ይችላል። ንጉሥ ሕዝብን፣ አገርን ወይም አንድ ከተማ ብቻ ሊገዛ ይችላል። * “መንግሥት” የሚለው ቃል፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት” በተሰኘው ሐረግ መሠረት መንፈሳዊ ግዛትን ወይም ሥልጣንን ማመልከትም ይችላል። * እግዚአብሔር የፍጥረት ሁሉ ገዢ ቢሆንም፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት” የሚለው ሐረግ በተለይ የሚያመለክተው በኢየሱስ ያመኑትና ለእርሱ ሥልጣን በተገዙት ላይ እርሱ ያለውን ገዢነት ወይም ሥልጣን ነው። * ሰይጣን በምድር ያሉ ብዙ ነገሮችን ለጊዜው የሚገዛበት፣ “መንግሥት” እንዳለው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። የእርሱ መንግሥት ክፉ ነው፣ “ጨለማ” ተብሎ ይጠራል።