# ዕጣን ዕጣን እሳት ላይ በሚደረግበት ጊዜ ደስ የሚል ሽታ የሚሰጥ ጣፋጭ መዓዛ ያላቸው ቅመሞድ ድብልቅ ነው። እነዚህ ቅመሞች ከዕፅዋት ክፍሎች የተገኙ ሲሆኑ፣ በጣም ጥቃቅን እስኪሆኑ ድረስ ይደቅቃሉ። * ለእርሱ መሥዋዕት የሚሆን ዕጣን እንዲያጨሱ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮአል። ዕጣኑ የሚቀመመው እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሁሉም እኩል መጠን ካላቸው አምስት ቅመሞች ነበር። የተቀደሰ ዕጣን በመሆኑ፣ ለሌላ ዓይነት ዓላማ እንዲውል አይፈቀድም ነበር። * ለዕጣን ማጨሻ ብቻ የተመደበ የወርቅ መሠዊያ ነበር። * በእያንዳንዱ የጸሎት ጊዜ ቢያንስ በቀን አራት ጊዜ ዕጣኑ መጨስ ነበረበት። * በተጨማሪም የሚቃጠል ሥጋ መሥዋዕት በሚቀርብበት ጊዜ ሁሉ ዕጣን መጨስ ነበረበት። * የዕጣን መጨስ ጸሎትንና ከሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር የሚወጣ አምልኮን ይወክላል። * ዕጣን የሚለውን ቃል ለመተርጎም ሌሎች መንገዶች፣ “ጣፋጭ ሽታ ያለው ቅመም” ወይም፣ “ጥሩ ሽታ ያላቸው ተክሎች” የተሰኙ ናቸው።