# ሰኮና ሰኮና ግመልን፣ ላምና በሬን፣ ፈረሶችን፣ አህዮችን፣ በጎችና ፍየሎችን የመሳሰሉ አንዳንድ እንስሳት ታችኛውን የእግራቸውን ክፍል የሚሸፍን ጠንካራ ነገር ነው። * ሰኮና በምራመዱበት ጊዜ ለእንስሳቱ እግር ይከላከላል። * ሰኮናቸው የተከፈለና የሚያመስኩ እንስሳት ለመብላት ንጹሕ መሆናቸን እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮአል።