# ዓሣ አጥማጆች ዓሣ አጥማጆች ለመግብ የሚሆናቸውንና ሸጠው ገንዘብ የሚያገኙበትን ዓሣ ከባሕር የሚያጠምዱ ሰዎች ናቸው። አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ዓሣ አጥማጆች ዓሣ የሚያጠምዱት በመረብ አማካይነት ነበር። * በኢየሱስ ከመጠራታቸው በፊት ጴጥሮስና ሌሎቹ ሐዋርያት ዓሣ ያጠምዱ ነበር። * የእስራኤል ምድር የተለያዩ ባሕሮች ባሉበት ቦታ በመሆኑ ስለዓሣ እና ዓሣ አጥማጆች ብዙ ማጣቀሻዎች አሉት። * ይህ ቃል፣ “ዓሣ የሚይዙ ሰዎች” ወይም፣ “ዓሣ በመያዝ ገንዘብ የሚያገኙ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።