# በለስ በለስ የበለስ ዛፍ ላይ የሚበቅል ትንሽና ጣፋጭ ፍሬ ነው። ሰዎች ትኩሱን፣ ቀቅለው ወይም አድርቀው በለስ መብላት ይችላሉ፣ ወይም ይከትፏቸውና እንደቂጣ አድርገው ይበሏቸዋል። * የበለስ ዛፎች ቁመት 6 ሜትር ድረስ ያድጋል፤ ሰፋፊ ቅጠሎቻቸው ጥሩ ጥላ ይሆናል። * እስራኤላውያን እዚያ ከመምጣታቸው በፊት ያበለስ ዛፍ ምድረ ከነዓን ውስጥ በጣም ጠቃሚ መብል ነበር። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በለስ ለምግብና ሌላም ገቢ ለማግኘት ዋና ምንጭ ነበር። * መጽሐፍ ቅዱስ የእስራኤልን መበልጸግ ወይም አለመበልጸግ ምልክት እንዲሆን በለስን በምሳሌያዊ መልኩ ይጠቀማል (1 ነገሥት 4፣25፤ ኤርምያስ 5፣17)