# ችጋር ችጋር በመላው አገር ወይም አካባቢ የምግብ እጥረትን የሚጨምር ጥፋት ሲስፋፋ ማለት ነው። * የዝናብ አለመኖርን፣ ጥሩ ያልሆነ የአየር ሁኔታን፣ የሰብል መቀጨጭ ወይም ተባዮችን በመሳሰሉ ተፈጥሮአዊ ምክንያቶች የተነሳ የምግብ እጥረት ይከሰታል። * ከጦርነት ወይም መልካም ካልሆነ አስተደድር የተነሣም የምግብ እጥረት ሊኖር ይችላል። * ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው በእርሱ ላይ ኀጢአት ያደረገ ሕዝብን ለመቅጣት እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ራብ እንዲኖር ያደርግ ነበር። * አሞጽ 8፣11 ላይ “ራብ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ለእነርሱ ባለመናገር ሕዝቡን ይሚቀጣበት ጊዜ እንደሚመጣ በሚያመለክት ምሳሌያዊ አነጋገር ነው።