# የሐሰት ምስክር፣ ጠማማ ምስክር፣ ሐሰተኛ ወሬ “ሐሰተኛ ምስክር” እና “ጠማማ ምስክር” ሰዎችን ወይም ሁኔታዎችን በተመለከተ እውነቱን የማይናገር ሰው ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ እንዲህ ሲደረግ የሚታየው በመደበኛ ፍርድ ቦታ ነው። * ሐሰተኛ ወሬ የሚባለው ሐሰተኛ ምስክር የተናገረው ነው። * “በሐሰት መመስከር” ሰዎችን ወይ ሁኔታዎችን በተመለከተ እውነት ያልሆነውን መናገር ነው። * አንድ ሰው እንዲቀጣ ወይም እንዲገደል ለማድረግ ሰዎች ሐሰተኛ ምስክሮችን ቀጥረው ስለነበረበት ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱስ በርካታ ታሪኮች አሉት።