# መቀደስ፣ ቅድስና መቀደስ ለአንድ ራሱን ለቻለ ዓላማ ወይም ተግባር አንድን ነገር መለየት ወይም መስጠት ማለት ነው። * ዳዊት ወርቁንና ብሩን ለጌት ቀደሰ። * ብዙውን ጊዜ፣ “ቅድስና” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ለተለየ ዓላማ አንድ ነገር የመለየት ደንብን ወይም ሥርዓትን ነው። * መሠዊያን የመቀደስ ሥርዓት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ማቅረብንም ይመለከታል። * ያህዌን ብቻ እንዲያመልኩና የእርሱን ከተማ እንዲጠብቁ በአዲስ መልኩ ቃል በማስገባት እንደ ገና የተገነቡትን የኢየሩሳሌም ቅጥሮች በመቀደሱ ሂደት ነህምያ እስራኤላውያንን መራቸው። ይህም በሙዚቃ መሣሪያዎችና በዝማሬ የታጀበ ምስጋና ለእግዚአብሔር ማቅረብንም አካትቶ ነበር። * “መቀደስ” የሚለው ቃል “ለአንድ ዓላማ መለየት” ወይም፣ “አንድ የተለየ ተግባር ለመፈጸም መሰጠት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።