# ማጽናት፣ ማረጋገጥ፣ ማጽኛ “ማጽናት” የሚለው ቃል አንድ ነገር እውነት ወይም እርግጥ ወይም አስተማማኝ መሆኑን መናገር ወይም መመልከት ማለት ነው። * ብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእነርሱ ጋር የገባውን ኪዳን እንደሚያጸና እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይናገራል። ይህም ማለት ለእነርሱ የገባውን ቃል እንደሚጠብቅና እንደሚፈጽም መናገሩ ነው። * አንድ ሰው የጻፈውን ማጽናት እርሱ የጻፈው እውነት መሆኑን መቀበል ማለት ነው። * የእምነት “ማጽኛ” እውነት መሆኑን በሚያረጋግጥ መልኩ ለሰዎች የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ማስተማር ማለት ነው። * “በመሐላ ማጽናት” አንድ ነገር እውነተኛ አስተማማኝ መሆኑን ጠንከር አድርጎ መናገር ወይም መማል ማለት ነው። * ማጽናት የሚለውን የመተርጎም፣ “እውነት መሆኑን መናገር” ወይም፣ “አስተማማኝነቱን መግለጥ” ወይም፣ “ከዚያ ጋር መስማማት” ማለት ይቻላል። በዐውዱ መሠረትም፣ “ማረጋገጥ” ወይም፣ “ቃልን መስጠት” ማለት ይቻላል።