# ሰረገላ በጥንት ዘመን ሰረገሎች በፈረሶች የሚጎተቱ ቀለል ያለ ክብደት ያላቸው ባለ ሁለት ተሽከርካሪ (ጎማ) መጓጓዣ ነበሩ። * ሰዎች ሰረገሎቹ ላይ በመቀመጥ ወይም በመቆም ሰዎች ለጦርነት ወይም ለመጓጓዣ ይጠቀሙባቸው ነበር። * በጦርነት ጊዜ ሰረገሎች ያሉት ሰራዊት በፍጥነትና በቀላሉ ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ ሰረገሎች በሌሉት ሰራዊት ላይ የበላይነት ይኖራቸው ነበር። * የጥንት ግብፃውያንና ሮማውያን በፈረሶችና በሰረገሎች በመጠቀም ይታወቁ ነበር።