# ዝግባ “ዝግባ” የሚለው ቃል ቀይ ቡናማ እንጨት ያለው ሾጣጣ ጫፍ ያለውን ግዙፍ ዛፍ ያመለክታል። እንደ ሌሎች ሾጣጣ ዛፎች ሁሉ እንደ መርፌ የሾሉ ቅጠሎች አሉት። * ብሉይ ኪዳን ይህ ዛፍ በብዛት ይበቅልበት ከነበረው ከሊባኖስ ጋር አያይዞ ስለ ዝግባ ዛፍ ብዙ ይናገራል። * የዝግባ ዛፍ የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ሲሠራ ጥቅም ላይ ውሏል። * መሥዋዕት ለማቅረብና ሰዎችን በማንጻት ሥርዓትም ጥቅም ላይ ይውል ነበር።