# የመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ፤ ሳምንት ሳምንት ሰባት ቀኖች ያሉት ጊዜ ነው። * በአይሁድ አቆጣጠር ስልት መሠረት ሳምንት የሚጀምረው ፀሐይ ቅዳሜ ከጠለቀችበት ጊዜ ይጀምርና በሚቀጥለው ቅዳሜ ፀሐይ እስከጠለቀችበት ጊዜ ይጀምርና በሚቀጥለው ቅዳሜ ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ድረስ ያለው ጊዜ ነው፥ * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዳንዴ፣ “ሳምንት” የሚለው ቃል ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ሰባት የጊዜ ክፍሎችን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል፤ ለምሳሌ ሰባት ዓመት። * “የሳምንቶች በዓል” ከፋሲካ ሰባት ሳምንት በኋላ የሚመጣ የመከር ጊዜ በዓል ነው። በዓለ ሃምሳ ተብሎም ይጠራል።