# ቅርጫት “ቅርጫት” እርስ በርስ ከተጠላለፉ ነገሮች የሚሠራ መያዣን ያመለክታል * በብሉይ ኪዳን ዘመን ቅርጫት የዛፎች ልጥ(ቅርፊት)፥ ቅርንጫፎችና ሐረጎችን ከመሳሰሉ ጠንካራ የተክል ውጤቶች ይሠራ ነበር * ቅርጫት መንሳፈፍ እንዲችል ውሃ በማያስገባ ነገር ይሸፈን ነበር * ሙሴ ሕፃን ልጅ በነበር ጊዜ እናቱ ውሃ የማያስገባ ቅርጫት ሠርታ እንዲንሳፈፍ አባይ ወንዝ ውስጥ ጥላው ነበር * በዚህ ታሪክ “ቅርጫት” ተብሎ የተተረጎመው ቃል ኖኅ የሠራውን ጀልባ ለማመልከት “መርከብ” ከተባለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው። በሁለቱም ዐውዶች ያለው የጋራ ትርጉም፥ “ የሚንሳፈፍ መያዣ ነገርን” ማመልከቱ ነው