# መጥረቢያ * መጥረቢያ ዛፍን ወይም እንጨትን ለመቁረጥና ለመፍለጥ የሚያገለግል መሣሪያ ነው * ብዙውን ጊዜ መጥረቢያ ረጅም የእንጨት እጀታ(መያዣ) እና ጫፉ ላይ የተያያዘ ብረት ይኖረዋል * በእናንተ አካባቢ መጥረቢያ የሚመስል ሌላ መሣሪያ ካላችሁ “መጥረቢያ” የሚለውን ቃል ስትተረጉሙ የዚያን መሣሪያ ስም ማስገባት ትችላላችሁ * ይህ ቃል መተርጎም የሚችልባቸው ሌሎች መንገዶች፥ “ዛፍ መቁረጫ መሣሪያ” ወይም “ብረት ያለበት የእንጨት መሣሪያ” ወይም፥ “ረጅም እጀታ ያለው እንጨት መቁረጫ መሣሪያ” የተሰኙትንም ይጨምራል * ከብሉይ ኪዳን ከምናየው አንድ አጋጣሚ አንድ የመጥረቢያ ብረት ወንዝ ውስጥ ወድቆ ነበር፤ ስለዚህ ያ የመጥረቢያ ብረት ከእንጨት እጅታው የሚላቀቅ ዓይነት ነበር ቢባል የተሻለ ይሆናል