# ዐመድ “ዐመድ” የሚለው የሚያመለክተው እንጨት ከተቃጠለ በኋላ የሚቀረውን ግራጫ ዱቄት መሳይ ነገርን ነው። ዋጋ ቢስ ውይም ጥቅም የሌለውን ነገር ለማመልከት ምሳሌያዊ በሆን መልኩ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥቅም ላይ ውሏል። * የ “ዐመድ ክምር” የዐመዶች ቁልል ማለት ነው። * በጥንት ዘመን ዐመድ ላይ መቀመጥ የሐዘን ወይም የለቅሶ ምልክት ነበር። * ሐዘን ሲያጋጥም ማቅ መልበስና ዐመድ ላይ መቀመጥ ወይም ርስ ላይ ዐመድ መነስነስ የዘመኑ ባሕል ነበር። * አንድ ሰው ጥቅም የሌለውን ነገር የሚይያሳድድ ከሆነ ተግባሩ፥ “ዐመድ እንደመብላት” ነው ይባል ነበር * አንዳንዴ መጽሐፍ ቅዱስ ስለዐመድ ሲናገር፥ “አፈር” በሚለው ቃል ይጠቀማል። ደረቅ መሬት ላይ የሚገኘውን በጣም የላመ ደቃቅ አቧራን ያመለክታል። * “ዐመድ” የሚለውን ቃል ሲተረጉሙ፥ እንጨት ከተቃጠለ በኋላ የሚቀረውን ለማመልከት ነው የትርጉም ሥራው ፕሮጀክት በሚጠቀምበት ቃል ተጠቀሙ