# የዕጣን መሠዊያ * የዕጣን መሠዊያ ከእንጨት ይሠራና ላዩና ጎኖቹ በወርቅ ይለበጣል። ግማሽ ሜትር ርዝመት ግማሽ ሜትር ስፋትና አንድ ሜትር ያህል ቁመት ነበረው። * መጀመሪያ ላይ መገናኛው ድንኳን ውስጥ ነበር የሚቀመጠው በኋላም ቤተ መቅደሱን ውስጥ ይቀመጥ ነበር። * በየጠዋቱና በየምሽቱ ካህን ላዩ ላይ ዕጣን ያቃጥላል። * “ዕጣን ማቃጠያ መሠዊያ” ወይም “የወርቅ መሠዊያ” ወይም፣ “ዕጣን ማቃጠያ” ወይም “የዕጣን ገበታ”ተብሎ መርጎምም ይቻላል።