# ነጻ ማድረግ “ነጻ ማድረግ” አንድ ሰው ከተከሰሰበት በደል ወይም ርኩሰት ነጻ መሆኑን በግልጽ መናገር ወይም ማወጅ ማለት ነው። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኃጢአተኛን ይቅር ማለትን አስመልክቶ ለመናገር ይህ ቃል ጥቅም ላይ ይውላል። * ብዙውን ግዜ ዐውዱ በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ያደረጉና በእርሱ ላይ ያመፁ ሰዎችን አለ አግባብ ነጻ ማድረግን ይመለከታል። * “ንጽህናን ማወጅ”ወይም “ከበደል ነጻ ማድረግ” ተብሎ መተርጎም ይችላል