# ዘካርያስ - (አዲስ ኪዳን) ዘካርያስ በኋላ መጥምቁ ዮሐንስን የወለደ የአይሁድ ካህን ነበር። * ዘካርያስ እግዚአብሔርን ይወድና ለእርሱም ይታዘዝ ነበር። * ዘካርያስና ሚስቱ ኤልሳቤጥ ልጅ እንዲወልዱ አጥብቀው ብዙ ዓመት ቢጸልዩም፣ መውለድ አልቻሉም ነበር። በጣም ባረጁ ጊዜ ግን እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ሰምቶ ልጅ ሰጣቸው። * የእርሱ ልጅ ዮሐንስ የመሲሑን መንገድ የሚያዘጋጅ ነቢይ እንደሚሆን ዘካርያስ ትንቢት ተናገረ።