# ቲርዛ ቲርዛ በጣም ጠቃሚ የከነዓናውያን ከተማ ነበረች፤ በኋላም የሰሜናዊው የእስራእል መንግሥት ጊዜያዊ ዋና ከተሞች አንዷ ሆና ነበር። * የቲርዛ ከተማ የምናሴ ነገድ በያዘው ክልል ውስጥ ነበር የምትገኘው። ከሴኬም ከተማ 10 ማይሎች ርቀት ላይ እንደ ነበረች ይታሰባል። * ቲርዛ ርስት እንዲሰጣችአው ከጠየቁ የምናሴ ሴቶች ልጆች አንዷ ነበረች፤ እንዲህ ያደረጉት በዘመኑ በነበረው ባሕል ርስት የሚካፈሉ ወንድሞች ስላልነበራቸው ነበር።