# ሲላስ፣ ስልዋኖስ ሲላስ በኢየሩሳሌም በነበሩ አማኞች መካከል መሪ ነበር * በኢየሩሳሌም የነበረችው ቤተ ክርስቲያን ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ እንዲሄድ ሲላስን መረጠች * በኋላ ላይ ለሰዎች ስለ ኢየሱስ ለማስተማር ሲላስ ከጳውሎስ ጋር ወደ ሌሎች ከተሞች ተጉዟል * ጳውሎስና ሲላስ በፊልጵስዩስ ከተማ ታስረው ነበር። እዚያ በነበሩ ጊዜ ሁሉ በእግዚአብሔር በመታመን እርሱን በመዝሙር ያመሰግኑ ነበር። እግዚአብሔር ከእስር ቤት አወጣቸው፤ የወህኒውንም ጠባቂ ለማዳን ተጠቀመባቸው