# ሰናክሬም ሰናክሬም ነነዌ ሀብታምና ተፈላጊ ከተማ እንድትሆን ታላቅ የአሦር ንጉሥ ነበር * ንጉሥ ሰናክሬም ከባቢሎንና ከይሁዳ መንግሥት ባደረጋቸው ጦርነቶች ይታወቃል * በጣም እብሪተኛና በያህዌ የተሳለቀ ንጉሥ ነበር * በንጉሥ ሕዝቅያስና በነቢዩ ኢሳይያስ ዘመን ሰናክሬም ኢየሩሳሌምን አጠቃ * ያህዌ የሰነክሬም ሰራዊት እንዲደመሰስ አደረገ * ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉት መጽሐፈ ነገሥትና መጽሐፈ ዜና መዋዕል በአገዛዝ ዘመኑ ስላደረጋቸው አንዳንድ ነገሮች ያመለክታሉ