# ሮቤል ሮቤል የመጀመሪያው የያዕቆብ ልጅ ነበር። እናቱ ልያ ትባላለች። * ወንድሞቹ ታናሽ ወንድማቸው ዮሴፍን ለመግደል ሲማከሩ፣ ከዚያ ይልቅ ጉድጓድ ውስጥ እንዲጥሉት በመናገር የዮሴፍን ሕይወት ያዳነ ሮቤል ነበር። * በኋላም ተመልሶ በመምጣት ሮቤል ዮሴፍን አዳነ ሌሎች ወንድሞቹ ግን በዚያ በኩል እያለፉ ለነበር ነጋዴዎች ለባርነት ሸጡት። * የሮቤል ዘሮች ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዱ ሆነዋል።