# ሮብዓም ሮብዓም ከንጉሥ ሰሎሞን ልጆች አንዱ ሲሆን፣ ሰሎሞን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ንጉሥ ሆኗል. * ሮብዓም የእስራኤልን ሕዝብ በሚያስመርር ሁኔታ በመናገሩ አሥሩ ነገዶች እርሱ ላይ ዐመፁ። ከዚህም የተነሣ የእስራኤል መንግሥት ለሁለት ተከፈለ፤ በሰሜን ያለው የእስራኤል መንግሥት ሲባል፣ በደቡብ ያለው የይሁዳ መንግሥት ተባለ። * ሮብዓም በእርሱ ታማኝ የሆኑ ሁነቱን ነገዶች በያዘው የይሁዳ መንግሥት ንጉሥ መሆኑን ቀጠለ። * ሮብዓም ለእግዚአብሔር የማይታዘዝ ክፉ ንጉሥ ነበር፤ የተለያዩ አማልክትንም ያመልክት ነበር።