# ፍልስጥኤም ፍልስጥኤም ምድረ ከነዓን ውስጥ በጣም ሰፊ የነበረው አካባቢ ስም ሲሆን፣ የምትገኘው በሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ ነበር። * ያ አካባቢ የሚገኘው በስተ ሰሜን ከኢዮጴ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ጋዛ በሚደርስ በጣም ለም የባሕር ዳርቻ ነበር። 64 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 16 ኪሎ ሜትር ስፋት ነበረው። * ፍልስጥኤም ውስጥ የሚኖሩ የዝወትር የእስራኤል ጠላት የሆኑት “ፍልስጥኤማውያን” በሚባሉት ሕዝብ ነበር።