# ፋራን የፋራን በረሐ ከግብፅ በስተምሥራቅና ከምድረ ከንዓን በስተደቡብ የሚገኝ ምድረበዳ ነበር። ፋራን የሚባል ተራራም ነበር፤ ምናልባትም ይህ ስም የሲና ተራራ ሌላ ስም ሊሆን ይችላል። * እነርሱን እንዲያባርር ሣራ አብርሃምን ካዘዘችው በኋላ ባርያይቱ አጋርና ልጇ እስማኤል በፋራን በረሐ ለመኖር ሄደው ነበር። * ሙሴ እስራኤልን እየመራ ከግብፅ በወጡ ጊዜ በፋራን በረሐ ውስጥ አልፈው ነበር። * ምድረ ከንዓንን እንዲስልሉና መረጃ እንዲያመጡ ሙሴ አሥራ ሁለት ሰዎችን ወደዚያ የላከው ፋራን ምድረበዳ ውስጥ ካለው ቃዴስ በርኔ ነበር። * የጺን ምድረበዳ በጣም ሰፊ የሆነው የፋራን በረሐ ክፍል ሊሆን እንደሚችል ይታሰባል።