# መርዶክዮስ መርዶክዮስ በፋርስ አገር ይኖር የነበረ አንድ አይሁዳዊ ስም ነው። በኋላ ላይ የፋርስ ንጉሥ የአርጤክስስ ሚስት የሆነችው የአጎቱ ልጅ የአስቴር ጠባቂ ነበር። * ቤተ መንግሥት ውስጥ እየሠራ እያለ ሰዎች ንጉሥ አርጤክስስን ለመግደል ሲመካከሩ ሰማ። ይህን በመናገሩ ንጉሡ ከሞት ተረፈ። * ከግዙ ጊዜ በኋላም መርዶክዮስ በፋርስ መንግሥት ውስጥ የነበሩ አይሁድን በሙሉ ለመግደል የወጣውን ዕቅድ ሰማ። ሕዝቧን ለማዳን ለንጉሡ አቤቱታ እንድታቀርብ አስቴርን መከራት።